ብቃት ያለው አስተዳደር

ሀገራት ልማትን በማረጋገጥ አዳጊና ተለዋዋጭ የሆነውን ፍላጎት ማሟላትና ኢኮኖሚያቸው በማይናወጥ መሰረት ላይ እንዲመሰረትና በቀጣይ ብልጽግናን እያረጋገጠ እንዲሄድ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህን ውጤት ለማስመዝገብ የዕድገት አቅሞችን በማሰባሰብ መረባረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ሀገራት ልማትን በማረጋገጥ አዳጊና ተለዋዋጭ የሆነውን ፍላጎት ማሟላትና ኢኮኖሚያቸው በማይናወጥ መሰረት ላይ እንዲመሰረትና በቀጣይ ብልጽግናን እያረጋገጠ እንዲሄድ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህን ውጤት ለማስመዝገብ የዕድገት አቅሞችን በማሰባሰብ መረባረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሀገራት በራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ አቅም አሰባስበው ያደጉበት መንገድ የተለያየ ቢሆንም በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ የግሉ ዘርፍ፣ መንግሥት እና የተለያዩ አደረጃጀቶች ተሳትፎ እና አሻራ በጉልህ ይታያል፡፡ በተከተሉትና በሚያቀነቅኑት የኢኮኖሚ ፖሊሲ መሰረት በማድረግ የእያንዳንዱ ዘርፍ አስተዋጽኦ እና የተሳትፎ ደረጃ የተለያየ ቢሆንም በየትኛውም ሀገር መንግሥት ጣልቃ ገብነት ሳይኖር በገበያ ብቻ ዕድገት ማግኘት እንደማይቻል የታወቀ ነው፡፡ በዚህ መሰረት በሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ቁልፍ የልማት እና የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ኃይል ሆነው ቆይተዋል፡፡
የአስተዳደሩ ራዕይም የልማት ድርጅቶችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በማስቻል ለባለድርሻ አካላት ዘላቂነት ያለው እሴትን መፍጠር ሲሆን፣ ይህ በዋናነት በልማት ድርጅቶች ያለን የመንግሥትንና የህዝብን ሀብት ለተሻለ የሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ማዋልን የሚገልጽ ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተገናኘ አስተዳደሩ ሀገራዊ ተልዕኮውን ለማሳካት በመቋቋሚያ ደንቡ የተሰጡትን አምስት ዋና ዋና ዓላማዎች እንዲተገብር የሚያስችሉ የረዥም ጊዜና የአጭር ጊዜ ስትራቴጂያዊ ዕቅዶችን ቀርጾ እየሰራ ሲሆን፣ በዚህ ተግባር ህልውናቸው ስጋት ላይ ወድቆ የነበሩ የልማት ድርጅቶች ወደ ትርፋማነት እንዲመጡ ተደርጓል፡፡ ወደ ትርፋማነት ከመምጣት ባለፈም በአሁኑ ሰዓት ሌሎች ሀገራዊ ተቋማትን በመደገፍ እና ከብር 1.5 ትሪሊዮን በላይ ሀብትን በማንቀሳቀስ በሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ የማይናቅ ሚናን እየተጫወቱ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ወቅት መንግሥት በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ያጋጠመውን ስብራቶች ለመጠገን የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሀግብር አዘጋጅቶ እየተገበረ ይገኛል፡፡ ከኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሀግብሩ ምሶሰሶዎች ውስጥ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሪፎርም አንዱ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ሀገራዊ ለውጥን እና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመቃኘት በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር እንዲሁም በመንግሥት የልማት ድርጅቶች የለውጥ ትግበራ መካሔድ ጀምሯል፡፡
ይህ ለውጥ ከሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ ከመዋቅራዊ ማሻሻያ እና ከፐብሊክ ፋይናንስ አንጻር ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች የሚጠበቅን ተግባር ከግምት ውስጥ ያስገባ እና የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሀግብሩን ሊደግፍ የሚችል ነው፡፡ በዚህ መሰረትም ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመዳሰስ የትኩረት መስኮች ተለይተው ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛል፡፡ የትኩረት መስኮቹ የልማት ድርጅቶችን ውጤታማና ተወዳዳሪ ከማድረግ፣ የድርጅት አመራር ውጤታማ እንዲሆን ከማስቻል፣ ተቋማዊ አቅምን ከመገንባት፣ ትራንስፎርሜሽንን ከመደገፍና ከማሳለጥ እና በልማት ድርጅቶች የኮርፖሬት ገቨርናንስና ፋይናንስ ሥርዓቶችን ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር ያተኮሩ ናቸው፡፡
የልማት ድርጅቶችን ተወዳዳሪ ለማድረግ ስልጣንን፣ ኃላፊነትና ተጠያቂነትን፣ ውሳኔ አሰጣጥን የገንዘብ ምንጭን፣ የካፒታል መዋቅርን፣ የሂሳብ አያያዝ እና ኢንቨስትመንትን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይጠበቃል፡፡ በሌላ አገላለጽ ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓትን ተግባረዊ ማድረግን ግድ ይላል፡፡ እነዚህን ጉዳዮች ለመመለስ የኮርፖሬት ገቨርናንስና ፋይናንስ ሥርዓቶች ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛል፡፡
አስተዳደሩ ጠንካራ የድርጅት አመራር መርሆዎችንና የአመራር ልምዶችን ተከትሎ፣ ፈጠራ በታከለበት አሰራር የልማት ድርጅቶች ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑና የሀገርን ኢኮኖሚ ከዚህ በተሻለ መልኩ እንዲደግፉ ለማድረግ እየሰራ ቢሆንም ይህ ተግባር የበለጠ ስኬታማ እንዲሆን የባለድርሻ አካላት ንቁ ተሳትፎ፣ ድጋፍና ትብብር ወሳኝ ሚናን እንደሚጫወት ይታመናል፡፡
ይህንን ቁልፍ ተግባር ለማከናወንም የልማት ድርጅቶችን አቅም መገንባት፣ ዓለማአቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እና በሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ያላቸው አስተዋጽኦ ደግሞ ከፍ እንዲል የማስቻል አቅጣጫዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው የሀገራዊ ብልጽና ጉዞውን የመደገፍ ተግባራት ሲከናወኑ ቆይተዋል፤አሁንም በመከናወን ላይ ናቸው፡፡
በመሆኑም የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ውጤታማና ተወዳዳሪ በማድረግ የሀገርን ኢኮኖሚ እንዲደግፉ ለማስቻልና የሀገር በቀል የኢኮኖሚው ማሻሻያ ዋና ግብ የሆነውን የኢኮኖሚ ስብራት የመጠገን ፣ምርትና ምርታማነትን የማሻሻል እና የግሉን ኢኮኖሚ ተሳትፎ የማሳደግ ዕቅድን በማሳካት ወሳኝ የሀገር ብልጽግና ጉዞን በጋራ ለማሳካት የባለድርሻ አካላት ከአስተዳደሩና ከልማት ድርጅቶች ጎን በመሆን በባለቤትነት መንፈስ እንድትሰሩ ጥሪዮን ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡
በጋራ የበለጸገች ሀገርን ለመጭው ትውልድ እናስተላልፋለን!
አመሰግናለሁ!

የህዝብ ሀብት ለህዝብ!

በስርዓት ዲዛይን ዘርፍ ስር:-

  • የኮርፖሬት አስተዳደር እና ፋይናንስ መሪ ሥራ አስፈፃሚ
  • ትራንስፎርሜሽን እና የአቅም ግንባታ መሪ ሥራ አስፈፃሚ
  • የፕራይቬታይዜሽን ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈፃሚ

የበላይ አስተዳደር

አስተዳደሩ PEHAን ለመምራት እንደ አስተዳደር እውነተኛ ልዕለ ስልጣን አለው።

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር

PEHA

PEHA

ገርጂ ኢምፔሪያል፣ አዲስ አበባ

Mon – Fri: 8:30 am – 5:30 pm

ጠቃሚ ሊንኮች

PEHA© 2024. All Rights Reserved