የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር አጭር መግለጫ

አስተዳደሩ ቀደም ሲል የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ይባሉ የነበሩ ሁለት ተቋማት በአዋጅ ቁጥር 412/96 ተዋህደው ከመሰረቱት ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ አደረጃጀቶችን አልፎ እዚህ የደረሰ ተቋም ነው፡፡ በጥር 13 ቀን 2014 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 1263/2014 መሰረት አሁን የሚጠራበትን ስያሜ ማለትም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ይዞ በህዳር 20 ቀን 2011 ዓ.ም በወጣው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 ሲቋቋም በደንብ ቁጥር 445/2011 ተሰጥቶት የነበረውን ተግባርና ኃላፊነት ይዞ ወደተግባር ገብቷል፡፡

የአስተዳደሩ ተልዕኮ፣

በዘመናዊ የኮርፖሬት ገቨርናንስና ፋይናንስ አመራር ልምዶችና ቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር ተግባራዊ በማድረግ የልማት ድርጅቶች ለሀገሪቱ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ ማሳደግ፣

የአስተዳደሩ ራዕይ፣

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በሀገርና በዓለማቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በማስቻል ለባለድርሻ አካላት ዘላቂነት ያለው እሴት መፍጠር፣

ዕሴቶች፣

የህዝብ ጥቅም፣ ልቀት፣ የቡድን ስራ፣ ፈጠራ። የሕግ የበላይነት።

Render Public Investment unto the People!

የPEHA የአስተዳደር ዋና ዓላማዎች፣ ሥልጣን እና ተግባራት።

  • የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ውጤታማ፣ ተወዳዳሪና አትራፊ ኢንዲሆኑ ዘመናዊ የኮርፖሬት አስተዳደርና ኮርፖሬት ፋይናንስ ሥርዓት መዘርጋትና ሥራ ላይ መዋሉን መከታተል፣
  • የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን አመራርና አስተዳደር መከታተል፣
  • በመንግሥት የልማት ድርጅቶችና አክሲዮን ማኅበራት ውስጥ መንግሥትን በመወከል የመንግሥት የባለቤትነት መብት ማስከበር፣
  • የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን አስተዳደር የመንግሥት የባለቤትነት፣ የተቆጣጣሪ እና የፖሊሲ አውጭውን አካላት ኃላፊነትና ሚናን በለየ መልኩ መተግበሩን ማረጋገጥ እና
  • በመንግሥት የልማት ፖሊሲ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ስምሪት መካካል የሚኖረውን ቅንጅት ማሳለጥ ናቸው፡፡
  • የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ስትራቴጂያዊና ዓመታ ዕቅድ መያዛቸውን ማረጋገጥ፣ ዕቅዶቹን ማፅደቅ፣ አፈጻጸማቸውን መቆጣጠር፣ መከታተል፣ መገምገም፣ የማስተካከያ እርምጃዎችን መውሰድ፤
  • የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ኦዲት ሪፖርቶች ማፅደቅ፣ በኦዲት ግኝቶች ላይ የእርምት እርምጃ መወሰዱን መከታተል፤
  • የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አፈጻጸም እና ተወዳዳሪነት እንዲሻሻል ማድረግ ዘመናዊ የኮርፖሬት አስተዳደርና የኮርፖሬት ፋይናንስ ሥርዓትን መዘርጋት፣
  • የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አስፈላጊ ችሎታ፣ ልምድ እና ዕውቀት ባላቸው ሰዎች የሚመሩበትን ሥርዓት መዘርጋት፣ ተግባራዊነታቸውን ማረጋገጥ፣
  • አዳዲስ የኢንቨስትመንት መስኮችን እና የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን በማጥናት እንዲፈቀድ ለመንግሥት የውሳኔ ሀሳብ ማቅረብ፣
  • የመንግሥት የልማት ድርጅቶች እንዲፈርሱ፣ እንዲዋሃዱ ወይም እንዲከፋፈሉ ለመንግሥት የውሳኔ ሀሳብ ማቅረብ፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ማድረግ፣
  • በገንዘብ ሚኒስቴር አጠቃላይ አመራርና አቅጣጫ በመመራት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወደ ግል እንዲዛወሩ የውሳኔ ሀሳብ ማቅረብ፣ ሲወሰንም በሥራ ላይ ባሉት አዋጅ ቁጥር 146/1991 እና 182/1992 ድንጋጌዎ መሠረት ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ፣
  • የትርፍ ድርሻ ክፍፍል ፖሊሲ ማዘጋጀት፣ በየበጀት ዓመቱ ከልማት ድርጅቶች ለመንግሥት ስለሚከፈል የትርፍ ድርሻ ክፍያ ለገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የውሳኔ ሀሳብ ማቅረብ፣ ተግባራዊነቱን መከታተል፣
  • የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሂሳብ ከመዝገብ መሰረዝን በሚመለከት ለገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ምክረሀሳብ ማቅረብ፣ አፈጻጸሙን መከታተል፣
  •  የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን አፈጻጸም እና ሁኔታ የሚያሳይ የመረጃ ሥርዓት ማደራጀት፣ የፋይናንስ አጠቃቀማቸው፣ የብድር አወሳሰድና አመላለሳቸውን በቅርበት በመከታተል የተጠቃለለ የሂሳብ ሪፖርት ለገንዘብ ሚኒስቴር ማቅረብ፣
  • የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ለምርምር እና ለፈጠራ በቂ በጀት እንዲመድቡ፣ የተገኘውን የምርምር እና የፈጠራ ውጤት እንዲያሰራጩ ሁኔታችን ማመቻቸት፣
  • የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የሚመለከቱ መረጃዎች ማዕከላዊ አስቀማጭ ሆኖ ማገልገል፣ የልማት ድርጅቶች አፈጻጸም የሚመለከቱ የውል መረጃዎችን ማሳወቅ፣
  • የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 25/1984 ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች ቦርድ የተሰጠው ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቅጥር እና ስንብት ላይ ይሁንታ መስጠት፣
  • የልማት ድርጅቶች ተሞክሮ የሚለዋወጡበትን መድረክ ማዘግጀት፣ የድርጅቶችን የአመራር አቅም ለማሳደግ የሚያስችሉ ሥልጠናዎች እንዲሰጡ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣
  • ከሕግ አግባብ ውጭ የተወሰዱ ንብረቶችን አስመልክቶ በእንጥልጥል ያሉ ጉዳዮችን በአዋጅ ቁጥር 572/2000 እና በሥራ ላይ ባሉ ሌሎች አግባብነት ባላቸው ሕጎች መሠረት አጣርቶ ውሳኔ መስጠት፣
  • ለአስተዳደሩ ተጠሪ የተደረጉ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን በሚመለከት በአዋጅ ቁጥር 25/1984 ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ተሰጥተው የነበሩ ሥልጣንና ተግባራትን በሥራ ላይ ማዋል እና
  • በመንግሥት የልማት ድርጅቶች እና በአክሲዮን ማኅበራት ውስጥ መንግሥት ያለውን የባለቤትነት መብት ለማስከበር የሚያስፈልጉ ተግባሮችን ማከናወን፣
  • አስተዳደሩ የራሱ ንብረት፣ ውሎችን ያጠናቅቃል፣
  •  የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የለውጡ ሂደት ሦስት መሰረታዊ ዓላማዎች 

ውጤታማ የመዋዕ ለነዋይ ሥራአመራር( Portfolio management)ስጋትን ለመቀነስ የሚያስችል የኢንቨስትመንት ስብጥር እንዲኖር ማድረግን ይመለከታል፡፡ የመዋዕ ለነዋይ ሥራአመራር( Portfolio management) ቁልፍ ነገሮች፡-

  • የኢንቨስትመንት ስትራቴጂ/ Investment strategy (ኢንቨስትመንትን ለመምራት የሚያስችሉ የአጭርና የረዥም ጊዜ የተጠቃለለ የአቀራረብ ስልት)
  • እሴት ፈጠራ ስትራቴጂ /value creation strategy (በተቋም ጠቅላላ ሀብት ላይ እሴትን የመፍጠር እና የመጠበቅ መዋቅራዊ ሂደት) እና
  • በአጠቃላይ መዋዕለነዋይ ላይ ያተኮረ ዝርዝር የስጋት አስተዳደር ፖሊሲ ማዕቀፍ እንዲኖር ማድረግ

የልማት ድርጅት ሥራአመራር(Enterprise management) የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዋነኛ ተግባር ሲሆን፣ መሰረታዊ ትኩረቱ ደግሞ የልማት ድርጅቶችን አፈጻጸም ማሳደግ ነው፡፡ ጤናማ የልማት ድርጅት ሥራአመራር የልማት ድርጅቶች በመዋዕለ ነዋያቸው/ሀብታቸው ላይ የእሴት ፈጠራ ስትራቴጂ ትግበራ ስለማከናወናቸው አስተዳደሩ የሚያረጋግጥበት ዋነኛ መንገድ ነው፡፡ የልማት ድርጅት አስተዳደር(Enterprise management) ሶስት ማዕቀፎች አሉት፡፡ እነዚህም፡-

  • የልማት ድርጅቶች ኮርፖሬት ገቨርናንስ (SOE corporate governance)
  • የልማት ድርጅቶች ሥራአፈጻጸም ሥረአመራር (Enterprise performance management) እና
  • የልማት ድርጅቶች ስጋት አስተዳደር (Enterprise risk management) ናቸው፡፡

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር መቋቋሚያ ደንብ ሰራተኞቹን የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ መሰረት ሠራተኞችን እንዲቀጥርና እንዲያስተዳድር ኃላፊነት ሰጥቶታል፡፡ በመሆኑም ህጉ አስተዳደሩ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሺን የሰራተኞችን ጥቅማጥቅም እና ደመወዝን ለማስፈጸም የወጡ መመሪያና ደንቦችን ተከትሉ እንዲሰራ ያስገድዳል፡፡ የተቋማዊ ሥራአመራር የሚያካትታቸው፡-

  • የአስተዳደሩን ተቋማዊ መዋቅር (PEHA organizational structure)
  • አስተዳደሩ የሚያከናውናቸውን የሠራተኛ ምልመላና ተፈላጊ ችሎታ ያላቸውን ሠራተኞች የማቆየት ተግባር( PEHA’s recruitment and retention of required skills)
  • የአስተዳደሩን የሥራ አፈጻጸም አስተዳደር( PEHA performance management) እና
  • የተጠቃለለ የለውጥ ሂደትን እና አተገባበር ዕቅድን( Transformation summary and implementation plans) ናቸው፡፡

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር

PEHA

PEHA

ገርጂ ኢምፔሪያል፣ አዲስ አበባ

Mon – Fri: 8:30 am – 5:30 pm

ጠቃሚ ሊንኮች

PEHA© 2024. All Rights Reserved