የኢትዮጵያ ልማት ባንክና የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሐሙስ ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ የድርጅቶቹ የቦርድና ማኔጅመንት አባላት ፣ከገንዘብ ሚኒስቴር የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች እና በአስተዳደሩ ተቋማቱን የሚከታተሉ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት ተገመገመ፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የብድር ተሰብሳቢ አፈጻጸሙ ከፍተኛ መሆን፣የገቢና የትርፍ ዕቅዱን ማሳካቱ፣የብድርና ተከፋይ አፈጻጸሙ ከፍተኛ መሆኑ፣የግብርና ብድር አገልግሎት እየተሻሻለ መምጣቱ እና በማህበራዊ አገልግሎት ያከናወናቸው ተግባራት በግምገማው አበረታች ውጤት ናቸው ከተባሉ አፈጻጸሞች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ባንኩ በሩብ ዓመቱ ብር 158.79 ሚሊዮን የህዳሴ ግድብ ቁጠባ እንዲቆጠብ ማድረግ ችሏል፡፡ከልማት ባንክ ቦንድ ሽያጭ ደግሞ ብር 1.5 ቢሊዮን በማከናወን ከዕቅዱ የበለጠ አፈጻጸም አስመዝግቧል፡፡ በውጭ ምንዛሪ ግኝት የ21.31 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተገኘ ሲሆን፣በውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ደግሞ36.78 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በማቅረብ 77 በመቶ ዕቅዱን አሳክቷል፡፡ ባንኩ በሩብ ዓመቱ ብር 4.25 ጠቅላላ ገቢ በማግኘት የብር 1.21 ቢሊዮን ትርፍ ከታክስ በፊት አግኝቷል፡፡
ኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት አማራጭ የገቢ ምንጮችን ለማሳደግ ያከናወናቸው ተግባራት፣በብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ህትመት እያከናወነው ያለ ተግባር፣ በለልዕክት ደህንነት፣በመልዕክት ትራፊክ መጠን እና በዓለም አቀፍ ሂያጅ መልዕክቶች ላይ ያከናወናቸው ተግባራት እንዲሁም ተወዳዳሪነትን ከግምት ውስጥ ያስገቡ የአሰራር ማሻሻያዎች ትግበራ አበረታች እንደሆኑ ተገምግመዋል፡፡ በሩብ ዓመቱ የብር 537 ሚሊዮን ጠቅላላ ገቢ በማግኘትም የዕቅዱን 106 በመቶ አሳክቷል፡፡
በግምገማው የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ተወካይ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ይርጋ እና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ትዕግስቱ አምሳሉ ድርጅቶቹ የሀገራዊ ሪፎርም ሂደቱ ውጤታማነት ማሳያ ተቋሞች እንደሆኑ የገለጹ ሲሆን፣ በቀጣይ መተግበር ስላለባቸው ጉዳዮችም አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

Previous በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ የሁለት ልማት ድርጅቶች አፈጻጸም ግምገማ ተካሔደ

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር

PEHA

PEHA

ገርጂ ኢምፔሪያል፣ አዲስ አበባ

Mon – Fri: 8:30 am – 5:30 pm

ጠቃሚ ሊንኮች

PEHA© 2024. All Rights Reserved