በህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን እና የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽንን የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ገመገመ፡፡
በግምገማው በቅድሚያ የታየው የትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሲሆን፣የኤሌክትሪክ አቅርቦት ማደጉ፣ የውጭ ሀገር ሽያጭ ማደጉን እና የ2016 በጀት ዓመት ሂሳብ ተዘግቶ ለኦዲት መቅረቡ በዋናነት ከተነሱ ስኬቶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡በሩብ ዓመቱ የኃይል ምርት ከዕቅዱ በላይ የተፈጸመ ሲሆን ፣ የኃይል ሽያጭም ከዕቅዱም ሆነ ካለፈው ዓመት ተመሳሳየ ወቅት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር ዕድገት አሳይቷል፡፡የኃይል ማመንጫ እና የኃይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክቶች ከዕቅዱ ከ80 በመቶ በላይ የፊዚካል አፈጻጸም አስመዝግበዋል፡፡በመሆኑም በሩብ ዓመቱ የ6,456 ጌጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ምርት ተመርቷል፡፡ይህ የዕቅዱን 117 በመቶ ነው፡፡የሩብ ዓመቱ የኃይል ማስተላለፍና ማከፋፈል ስራዎች በቁልፍ አፈጻጸም መለኪያዎች ሲመዘኑ አፈጻጸማቸው በአማካይ 89 በመቶ እንደሆነ ተገምግሟል፡፡የኃይል ሽያጭ ደግሞ 6,004 ጌጋ ዋት ሲሆን፣ ይህም ከዕቅዱ 114 በመቶ ነው።
በኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የሩብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ የተሻለ ገቢ ማግኘት መቻሉ፣የስልጠና ማዕከል ማዘጋጀቱ፣በኮንስትራክሽን ዘርፍ ወደሥራ መግባቱ እና በንብረት አያያዝ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት አበረታች እንደሆኑ ከታዩ ተግባራት መካከል ይገኙበታል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ገቢ ሊያመነጩ የሚችሉ አዳዲስ ፕሮጀክቶች ለመተግበር ጥረት ሲያደርግ የቆየ ሲሆን፣በሩብ ዓመቱ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ተሰማርቶ እየሰራ ካለው የሮቤ-ጋሴራ-ጊኒረ የ60-120 ኪ.ሜ ጠጠር መንገድ ውስጥ የ15 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድ ጥገና ለማከናወን አቅዶ የ12.44 ኪ.ሜ መንገድ መጠገን ወይም የዕቅዱን 81.3 በመቶ አከናውናል፡፡ በንብረት አያያዝ ላይ በመስራትም የብር 148.6 ሚሊዮን ግምት ያላቸውን ንብረቶች ማሰባሰብ ችላል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ከዚህ በፊት ከነበሩበት ተግዳሮቶች በመውጣትም አበረታች ገቢ አግኝቷል፡፡የማህበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት በማቀድ ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የብር 500 ሺህ ድጋፍ አድርጓል፡፡የሀብት አጠቃቀም እና የወጪ ቅነሳ አሰራር ስርዓትን በመከተል የብር 4. 6 ሚሊዮን ብር መቀነስ ችሏል፡፡
በግምገማው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ተወካይ ዋና ዳይሩክተር አቶ ዝናቡ ይርጋ እና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ምክተትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ትዕግስቱ አምሳሉ የተቋማቱን አመራሮች ሀገራዊ ዓላማን ይዘው በጥንካሬ ድርጅቶቹ ከነበሩባቸው ተግዳሮቶች እንዲወጡ እያበረከቱት ላለው ጉልህ አስተዋጽኦ ምስጋና አቅረበዋል፡፡

Previous አስተዳደሩ የሁለት ኮርፖሬሽኖችን ዕቅድ አፈጻጸም ገመገመ

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር

PEHA

PEHA

ገርጂ ኢምፔሪያል፣ አዲስ አበባ

Mon – Fri: 8:30 am – 5:30 pm

ጠቃሚ ሊንኮች

PEHA© 2024. All Rights Reserved